ሎሚ መልቲ ሚዲያ

 ሌሎች የሃገር ውስጥና የውጪ የሚዲያ ተቋማት እስካሁን ድረስ ያልሸፈኗቸው እና ለህብረተሰቡ ጆሮ ያላበቋቸው የማህበረሰቡ ችግር ፈቺ ሃሳቦችና የአሰራር ስልቶች፣ የአዲሱ ትውልድ የፈጠራ ውጤቶች በአዲስ አቀራረብ አዘጋጅቶ ማቅረብ፤
 የፈጠራ ኢንዱስትሪው፣ የሙዚቃ፤ የፊልም፤ የሥነ-ፅሁፍ፤ የቴሌቪዥንና ሬዲዮ፤ የመድረክ ድራማዎች እና በዘመኑ ቴክኖሎጂ የታገዙ የመዝናኛ ዝግጅቶች በዘርፉ ባለሙያዎች ሙሉ ተሳትፎ እንዲቀርቡ በማድረግ ህብረተሰቡና የዘርፉ ባለሙያዎቹ ተጠቃሚ ማድረግ፡፡
 በጥናት የታገዙ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን፤ የሬዲዮና የቴሌቪዥን የማስታወቂያ ስራዎችን፤ የማርኬቲንግና ፕሮሞሽን ክንውኖችን፤ የህዝብ ግንኙነትና ሁነት ዝግጅቶችን፤ የብራንዲንግና ሪብራንዲንግ ስራዎችን በዘመኑ ቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲከናወኑ በማድረግ በዘርፉ የሚታየውን የአቅርቦትና ፍላጎት ክፍተት መሙላት፡፡
 በሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን፣ በማርኬቲንግና ፕሮሞሽን እና በመዝናኛ ኢንዱስትሪው ዙርያ ጥናትና የማማከር አገልግሎት መስጠት፤
 በዲጂታል ሚዲያ እና የህትመት ሥራዎች ላይ የህትመት ስርጭት ሥራ ማከናወንና፣ የጥናትና የማማከር አገልግሎት መስጠት፣

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top